Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የተሽከርካሪ ሰሌዳን እናስጨርሳለን ከሚሉ ግለሰቦች ህብረተሰቡ ራሱን እንዲጠብቅ ተጠየቀ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የተሽከርካሪ ሰሌዳን ህትመትና ስርጭት ከትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር በውክልና ተረክቦ ስራውን በማከናወን ላይ ያለው የፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት ጉዳይ እናስፈፅማለን በሚል ገንዘብ ከሚጠይቁ ግለሰቦች ህብረተሰቡ መጠንቀቅ እንደሚገባ ተገለጸ፡፡
 
የድርጅቱ የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን አምባቸው በሰጡት መግለጫ ድርጅቱ የተሽከርካሪ ሰሌዳን በህጋዊ መንገድ ከክልልና ከአስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮዎች ጋር በመተባበር በመስጠት ላይ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
 
የተፈጠረው የህትመት ስርጭት አከናዋኝ የባለቤትነትን ለውጥ በመጠቀም አንዳንድ ግለሰቦች የሰሌዳ ቁጥር የሚፈልጉ አሽከርካሪዎችን ጉዳይ እናስፈፅማለን በማለት የማታለል ተግባር እየፈፀሙ መሆኑንም ነው ያመላከቱት፡፡
 
እነዚህን ወንጀለኞች ለማጋለጥ ድርጅቱ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመስራት ላይ መሆኑን የገለፁት ዳይሬክተሩ÷ ሰሌዳ ለሚጠይቁ በክልልና በአስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮዎች አማካኝነት ህጉን ተከትሎ እየተሰጠ በመሆኑ ምንም ዓይነት የጥሬ ዕቃም ሆነ የህትመት ችግር እንደሌለ ገልፀዋል፡፡
 
የፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት ስራውን ከመረከቡ በፊት በቀን በአማካኝ 300 የሰሌዳ ቁጥሮችን ይታተሙ እንደነበር ገልፀው÷ በአሁኑ ጊዜ የዕረፍት ቀናትን ጨምሮ በምሽት ክፍለ ጊዜ ህትመትና ስርጭት በመከናወኑ በቀን በአማካይ ከ3 ሺህ በላይ የተሸከርካሪ ሰሌዳዎችን በመታተም ላይ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
 
ጉዳይ እናስፈፅማለን በማለት ገንዘብ የሚጠይቁ ግለሰቦች ሲያጋጥሙት ህብረተሰቡ ለፖሊስ እንዳለበት አሳስበዋል፡፡
 
ድርጅቱ በተቀላጠፈና በአጭር ጊዜ በህጋዊ መንገድ የሁሉንም ዓይነት ተሽከርካሪዎች የሰሌዳ ቁጥር እያተመ በማሰራጨትላይ መሆኑን መግለጻቸውንም ከቢሮው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version