Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በደብረ ብርሃን ከተማ በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የተገኘ ከ3 ሺህ በላይ ጥይት ተያዘ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በደብረ ብርሃን ከተማ ጠባሴ አካባቢ በተደረገ የኬላ ፍተሻ 1 ሺህ 937 የክላሽ እና 1 ሺህ 94 የብሬን ጥይት በአጠቃላይ 3 ሺህ 31 ጥይት ትናንት ከምሽቱ 2 ሰዓት ላይ በቁጥጥር ስር ውሏል።
 
ጥይቱ በቁጥጥር ስር የዋለው ሽንኩርት በጫነ አይሱዙ መኪና ደብቆ በመጫን ለማለፍ ሲሞከር ነው።
 
የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ሰላም እና ህዝብ ደህንነት ሃላፊ አቶ ዳንኤል እሸቴ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለፁት÷ አሽከርካሪውና አንድ ሌላ ግለሰብ በወንጅሉ ተጠርጥረው ተይዘው ተጨማሪ ምርመራ እየተደረገባቸው ነው።
 
በዘላለም ገበየሁ
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version