Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የተለያዩ ተቋማት ለሰራዊቱና ለተፈናቃዮች ከ29 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 2፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የተለያዩ ተቋማት ለመከላከያ ሰራዊት እና ከመኖሪያ ቀያቸው ለተፈናቀሉ ዜጎች ከ29 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጣ የአይነት ድጋፍ አድርገዋል።
 
የስራና ክህሎት ሚኒስቴር ከአራቱ ተጠሪ ተቋማት ጋር በመተባበር ለመከላከያ ሰራዊት እና ለተፈናቀሉ ወገኖች የ25 ሚሊየን ብር ቁሳቁስና የደረቅ ምግብ ድጋፍ አድረጓል።
 
ድጋፉን የስራና ክህሎት ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል ለሰሜን ሸዋ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ሲሳይ ወልደ አማኑኤል አስረክበዋል።
 
በተመሳሳይ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በአፋር ክልል በተካሄደው ሀገርን የማዳን ዘመቻ ከፍተኛ ተጋድሎ ያደረጉ ወገኖችን ለመደገፍ በሠመራ ዩኒቨርሲቲ በኩል ከ1 ሚሊየን 521 ሺህ 550 ብር በላይ የሚያወጡ የምግብ፣ የአልባሳት እና ቁሳቁስ ድጋፍ አበርክቷል።
 
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮም በከተማዋ የሚገኙ የትምህርት ተቋማትን በማስተባበር በህግ ማስከበርና በህልውና ዘመቻው ጉዳት ለደረሰባቸው የሰራዊቱ አባላት ከ3 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጡ 500 በጎችን ድጋፍ አድርጓል።
 
በሰላም አሰፋ እና አሊ ሹምባህሪ
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version