አዲስ አበባ፣ታህሳስ 2፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ነዋሪዎች፣የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ሰራተኞች እና የምዕራብ ወለጋ ዞን የጋንጂ ወረዳ የመንግስት ሰራተኞች የዘማች ቤተሰቦችን ሰብል ሰበሰቡ፡፡
የአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በጎ ፈቃደኛ ወጣቶችና ነዋሪዎች በሰበታ አዋስ ወረዳ በመገኘት የዘማች ቤተሰብ ሰብል ሰብስበዋል፡፡
ባለቤታቸው “ሁሉም የሚያምረው ሀገር ሰላም ስትሆን ነው” በማለት መዝመታቸውን የሚገልጹት ወ/ሮ ቢሪ ወርቁ÷ የደረሰ ሰብላቸው በአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በጎ ፈቃደኛ ወጣቶችና ነዋሪዎች መሰብሰቡ ከልብ እንዳስደሰታቸው ገልጸዋል።
የዘማች ቤተሰቦችን በመደገፍ ህብረተሰቡ እያደረገጋለው የደጀንነት ተግባር ተጠናክሮ መቀጠሉን የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አባወይ ዮሐንስ ገልጸዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ሰራተኞች እንዲሁ በሸኖ ከተማ ቅንብቢት ወረዳ የዘማች አርሶ አደር ቤተሰቦችን ያልተሰበሰቡ ሰብሎችን በመሰብሰብ እና ቤተሰቦቻቸውን ለማገዝ ቦታው ድረስ በመገኘት የደረሱ ሰብሎችን የመሰብሰብ ስራ አከናውነዋል።
በተመሳሳይ በምዕራብ ወለጋ ዞን የጋንጂ ወረዳ የመንግስት ሰራተኞች እና የእናት ኮሌጅ ጦራ ካምፓስ ተማሪዎችና ሰራተኞች የደረሰ ሰብል እና ቡና በመሰብሰብ ለዘማች ቤተሰቦች ድጋፍ አድርገዋል፡፡
የምዕራብ ወለጋ ዞን የጋንጂ ወረዳ ዋና አስተዳደሪ አቶ እንደሻው ሾሬ እንዳሉት÷ በምዕራብ ወለጋ ዞን የጋንጂ ወረዳ የዘማች ቤተሰቦች ደረሰ ቡና በተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፎ እየተለቀመ ነው።
ከዘማች ቤተሰቦች በሰጡት አስተያየት፥ “ተማሪዎቻችን የዘማች ቤተሰብን ሰብል በመሰብሰብ ደጀንነታቸውን አሳይተዋል እኛም በተማሪዎቻችን ኮርተናል” ብለዋል፡፡
የእናት ኮሌጅ ከ1 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር ባላይ ለመከላከያ ሰራዊት ድጋፍ ማደረጉና ለ10 የዘማች ቤተሰብ ልጆች ደግሞ ነጻ የትምህርት እድል መስጠቱም ተመላክቷል።
ድጋፉ የተደረገላቸው ቤተሰቦችም ለተደረገላቸው ድጋፍ አመስግነው፥ የህልውና ዘመቻው አካል በመሆናቸው ኩራት እንደተሰማቸው መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

