Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በውጪና በክልሉ የሚገኙ የሶማሌ ክልል ዳያስፖራዎች በእውቀትና የሙያ ሽግግር ስራዎች ላይ እንዲሳተፉ ጥሪ ቀረበ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል መንግስት በአሁኑ ወቅት የክልሉን ህዝብ ህይወት ለማሻሻል እያደረገ የሚገኘውን ጥረት ለማሳካት የክልሉ ዳያስፖራዎች ሙያና እውቀታቸውን በማሸጋገር የበኩላቸውን አስተዋፅኦ እንዲያበረክቱ ጥሪ ቀርቧል።

የሶማሌ ክልል የኢንቨስትመንትና ኢንዱስትሪ ቢሮ በክልሉ ዳያስፖራዎች የሙያና የእውቀት ሽግግር ላይ ያተኮረ ስብሰባ በጅግጅጋ ከተማ አካሂዷል።

በመድረኩ ላይ የክልሉ የኢንቨስትመንትና ዳያስፖራ ቢሮ አመራሮች ፥ በክልሉ የሚገኙ ዳያስፖራ አባላትና ከተለያዩ የትምህርት ተቋማት የተውጣጡ ሀላፊዎችና ምሁራን ተሳትፈዋል።

የሶማሌ ክልል የኢንቨስትመንትና የዳያስፖራ ቢሮ ምክትል ሀላፊ ወ/ሮ ዘይነብ ሀጂ በዚህ ወቅት እንዳሉት ÷ በተለያዩ የአለም ክፍሎችና በሀገሪቱ የሚገኙ ዳያስፖራዎች ያላቸውን እውቀትና ሙያ በማሸጋገር የክልሉ ህዝብ ተጠቃሚ የሚሆንበት ሁኔታ መፈጠር እንዳለበት አንስተዋል።

ከለውጡ ወዲህ በክልሉ በተፈጠረው ምቹ ሁኔታ በመጠቀም የክልሉ ዲያስፖራዎች 3 ቢሊየን ብር በሚደርስ ካፒታል ባከናወኗቸው የተለያዩ የኢንቨስትመንት ስራዎች ህዝቡ ተጠቃሚ መሆኑን የጠቆሙት ምክትል ሃላፊዋ፥ በቀጣይም በክልሉ ሁለንተናዊ ልማት ላይ የክልሉ ዳያስፖራዎች ተሳትፎ ሊጠናከር ይገባል ብለዋል።

ምክትል ሃላፊዋ የክልሉ መንግስት በአሁኑ ወቅት የክልሉን ህዝብ ህይወት ለማሻሻል እያደረገ የሚገኘውን ጥረት ለማሳካት የክልሉ ዳያስፖራዎች ሙያና እውቀታቸውን በማሸጋገር የበኩላቸውን አስተዋፅኦ እንዲያበረክቱ ጥሪ አቅርበዋል።

የክልሉ ተወላጅ ዳያስፖራዎች በተለያዩ መስኮች ተሳትፏቸውን ለማጠናከርና የሚያስፈልጋቸውን ድጋፍ ለማድረግ የክልሉ መንግስት ከምንጊዜውም በላይ በቁርጠኝነት እንደሚንቀሳቀስ በመድረኩ ላይ ተጠቁሟል ።

በመድረኩ የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ የተለያዩ ጥናታዊ ፅሁፎች ቀርበው ውይይት እንደተደረገባቸው የሶማሌ መገናኛ ብዙሃን ኤጀንሲ ዘግቧል ።

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version