Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በአሜሪካ አምስት ግዛቶችን የመታው ሃይለኛ አውሎ ንፋስ ከባድ ጉዳት አደረሠ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በዩናይትድ ስቴትስ አምስት ግዛቶችን የመታው ከባድ አውሎ ንፋስ 80 ሰዎችን ሲገድል መንደሮችን አውድሟል።

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ከአውሎ ንፋሱ አደጋ ጋር በተያያዘ በኬንታኪ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ያወጡ ሲሆን፥ የተጎዱትን ግዛቶች ለመደገፍ ቃል መግባታቸው በዘገባው ተመላክቷል።
በአደጋው ከሞቱት 80 ሰዎች ውስጥ 70ዎቹ የኬንታኪ ነዋሪዎች እንደሆኑ ነው የተገለፀው፡፡
ጉዳቱ ሊጨምር ይችላል የሚል ስጋት እንዳለም ተመልክቷል።
በአንድ ሌሊት ይህን ያህል የአሜሪካ ክፍል ያወደመው ይህ አውሎ ነፋስ በሀገሪቱ ታሪክ ውስጥ ከተፈጠሩት አውሎ ንፋሶች ትልቁ ነው ሲሉ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ተናግረዋል፡፡
የአደጋውን ተፅዕኖ ለመቀነስ የሚቻለውን ሁሉ እናደርጋለን ሲሉ ፕሬዚዳንቱ ቃል ገብተዋል፡፡
ለአደጋው መከሰት መንስኤ የአየር ንብረት ለውጥ ነው ብለው ያምናሉ ወይ? ተብለዉ ለተጠየቁት ጥያቄም በዚህ ዙርያ ምንም የምለው ነገር የለኝም፤ በጉደዩ ዙርያ የአካባቢ ጥበቃ ኤጀንሲ ጋር እነጋገራለሁ ነው ያሉት ፕሬዜዳንት ጆ ባይደን፡፡
የሙቀት መጨመር ሁሉም ነገር እንደሚቀይር ሁላችንም እናውቃለን ያሉት ፕሬዚዳንቱ ምክንያቱ እሱ ነው ብዬ ለመደምደም ግን እቸገራለሁ ሲሉ ተደምጠዋል፡፡
አደጋው በተከሰተባቸው አካባቢዎች ጉብኝት እንደሚያደርጉም ቃል መግባታቸውን ቲ አር ቲ ዘግቧል።
በአመለወርቅ ደምሰው
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version