አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ(ኢመደኤ) “ከሳይበር እስከ ግንባር” በሚለው መርሀ ግብሩ መሰረት በወሎ ግንባር በመገኘት ለመከላከያ ሰራዊት የዓይነት ድጋፍ አደረገ።
በግንባር በመገኘት ለሰራዊቱ ድጋፉን ያስረከቡት የኢመደኤ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሹመቴ ግዛው፥ ኢመደኤ እና መከላከያ ሚኒስቴር በተለያዩ ጉዳዮች በጋራ ስራዎችን እንደሚሰሩ አንስተዋል፡፡
ዋና ዳይሬክተሩ ፥ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ አቅማችሁ የቻለ ሁሉ ተከተሉኝ ባሉት መሰረት “ከሳይበር እስከ ግንባር” የሚል መርሀ ግብር በመቅረጽ ወደ ተግባር መገባቱን ጠቁመዋል።
ኤጀንሲው የኢትዮጵያን ዲጂታል ሉአላዊነት ለማስጠበቅ ከፍተኛ ስራዎች እየሰራ መሆኑን የገለጹት ዶክተር ሹመቴ ፥ ከዚህ ጎን ለጎን በማህበራዊ ጉዳዮች ንቁ ተሳታፊ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
በማሳያነትም ከፍተኛ አመራሩ እና አባላቱ በየሶስት ወሩ ሳያቋርጡ ለመከላከያ ሰራዊት የደም ልገሳ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል።
በዚህ መርሃ ግብር በደብረ-ብርሃንና አዲስ አበባ ለሚገኙ በጦርነቱ ጉዳት ለደረሰባቸው የሰራዊት አባላት የምሳ ግብዣ ፤ በደብረ-ብርሃን ለሚገኙ ከቀያቸው ለተፈናቀሉ ሴቶች፣ ህጻናት እና አቅመ ደካሞች የቁሳቁስ ድጋፍ መደረጉን ዶ/ር ሹመቴ ጠቁመዋል።
በድጋፍ መርሃ ግብሩ የተገኙት የሰባተኛ እዝ የቀለብ እና ንብረት ክፍል ሃላፊ ኮሎኔል ሙስጠፋ የሱፍ በበኩላቸው፥ ኢመደኤ በሳይበሩ ዓለም የሀገርን ሉዓላዊነት ለማስጠበቅ ከሚያደርገው ጦርነት፣ ለመከላከያ ከሚያስታጥቀው የቴክኖሎጂ ምርቶች ባሻገር ለመከላከያ ሰራዊቱ ወገንተኝነቱን ለማሳየት ግንባር ድረስ ድጋፍ ይዞ በመመጣቱ አመስግነዋል።
ኢመደኤ በመጀመሪያ ዙር “ከሳይበር እስከ ግንባር” በሚለው መርሃ ግብሩ ከ3ነጥብ 2 ሚሊየን ብር ዋጋ ያላቸው ድጋፎችን ከአዲስ አበባ እስከ ግንባር ላሉ ወግኖች ድጋፍ ማድረጉን ከኤጀንሲው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

