Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የምስራቅ ሐረርጌ አርሶ አደሮች የግብርና ግብአቶች በጊዜ እንዲደርሷቸው ጠየቁ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በምስራቅ ሐረርጌን ዞን በጎሮጉቱ ወረዳ ስንዴን በመስኖ ማምረታቸው አበረታች ውጤት እንዳስገኘላቸው አርሶአደሮች ተናገሩ፡፡
በወረዳው በዘንድሮው በጋ በመስኖ ልማት 500 ሄክታር መሬትን በስንዴ ለማልማት እየተሠራ ሲሆን÷ ከዚህ ውስጥም በ230 ሄክታር መሬት ላይ የቅድመ ዝግጅት ስራ ተጠናቆ ለዘር ዝግጁ መሆኑ ተመላክቷል።
የጎሮጉቱ ወረዳ ግብርና ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ከሊፋ ካሊድ፥ አርሶ አደሮቹ ዝናብን ጠብቀው በዓመት አንድ ጊዜ ሲያመርቱ መቆየታቸውን ጠቁመው፥ በዚህም የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ ይቸገሩ እንደነበር ተናግረዋል፡፡
አሁን ላይ የግብርና ባለሙያዎች ስንዴ በመስኖ እንዴት ማምረት እንደሚቻል ስልጠና በመስጠታቸውና አርሶ አደሮቹም ይህንኑ መተግበር በመጀመራው ውጤቶች እየተመዘገቡ መሆኑን አስታውቀዋል።
የወረዳው አርሶአደሮች በበኩላቸው በተሰጣቸው ስልጠና መሰረት ስንዴ ለማምረት ማሳቸውን በማዘጋጀት ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል።
ከዚህ ባለፈም ምርታማነትን ለማሳደግ እንዲረዳ የምርጥ ዘር እና የግብርና ግብአቶች በጊዜ እንዲደርሷቸው ጠይቀዋል፡፡
የጎሮጉቱ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ አህመዲን ሶፊያን በበኩላቸው፥ የአርሶ አደሮቹን ምርትና ምርታማነት በማረጋገጥ ከተረጂነት ለማላቀቅ የተቀናጀ ስራ እየተሰራ ነው ብለዋል።
በእዮናዳብ አንዱዓለም
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version