Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ኢትዮጵያውያን የገጠመንን ተግዳሮት ሁሉ ታግለን የምናሸንፍ ህዝቦች መሆናችንን ዛሬም በተግባር አረጋግጠናል – አቶ እርስቱ ይርዳ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያውያን በአገራቸው ጉዳይ የማይደራደሩና የገጠመንን ተግዳሮት ሁሉ ታግለን የምናሸንፍ ህዝቦች መሆናችንን ዛሬም በተግባር አረጋግጠናል ሲሉ የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እርስቱ ይርዳ ገለጹ።

የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች በወቅታዊ አገራዊና ክልላዊ ጉዳዮች ዙሪያ በሐዋሳ ከተማ እየተወያዩ ነው።

ኢትዮጵያን ከሁለንተና ብልጽግና በመንቀል በጦሪነት አዙሪት ለማቆየት የውጭና የውስጥ ኃይሎች የከፈቱብንን የህልውና ጦርነት ለመመከት ኢትዮጵያውያን ያሳዩት አንድነትና ጽናት የሚደነቅ መሆኑን ርዕሰ መስተዳድሩ ልጸዋል።

በህልውና ዘመቻው የኢትዮጵያን የግዛት አንድነትና ሉዓላዊነት ለማስጠበቅ ከተጀመሩ ስራዎች ጎን ለጎን ዘላቂ ሠላምና ሁለንታዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ የተጀመረው ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ነው ያመላከቱት።

ዛሬ በተጀመረው የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች መድረክ የክልሉ ካቢኔ አባላት፣ ሌሎች ከፍተኛ አመራሮችና የዞንና የልዩ ወረዳ አስተባባር አመራሮች እየተሳተፉ ነው።

መድረኩ ዝርዝር አገራዊና ክልላዊ ጉዳዮችን አንስቶ በመወያየት ቀጣይ አቅጣጫዎችን ያስቀምጣል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከክልሉ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version