አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን በ5 ወራት ውስጥ ከ741 ነጥብ 9 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ መስብሰቡን ገለፀ ።
ባለስልጣኑ በ2014 በጀት ዓመት 5 ወራት 776 ሚሊየን 350 ሺህ 677 ብር ገቢ ለመሰብሰብ አቅዶ 741 ሚሊየን 987 ሺህ ብር በላይ በመሰብሰብ የዕቅዱን 96 በመቶ ማሳካት መቻሉን አስታውቋል።
ገቢው የተሰበሰበው በውሃ አገልግሎት ዘርፍ ከሚሠጡ የውሃ ሽያጭ፣ የቆጣሪ ግብር፣ ከውሃ መስመር ቅጥያ ፣በፍሳሽ አገልግሎት ዘርፍ ከፍሳሽ ማንሳት አገልግሎትና ከሌሎች ተጨማሪ አገልግሎቶች መሆኑ ታውቋል፡፡
ባለስልጣኑ በበጀት ዓመቱ ከ1 ቢሊየን 705 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ ለመሠበሰብ ዕቅድ ይዞ እየሠራ መሆኑን ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

