አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው ህወሓት በከፈተው ጦርነት ምክንያት ተቋርጦ የነበረው የሀርቡ ከተማ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ጥገና ተደርጎለት ወደ አገልግሎት ገብቷል።
በሀርቡ ከተማ ተቋርጦ የነበረው የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተመልሶ የተገናኘው በአማራ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት የደሴ ዲስትሪክት ሰራተኞች የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መስመሮችን ለመጠገን ባደረጉት ከፍተኛ ርብርብ መሆኑን የዲስትሪክቱ ዳይሬክተር አቶ ሀብቱ አበበ አስታውቀዋል፡፡
አቶ ሀብቱ አክለውም ÷ ጃማ እና ወረኢሉ ከተሞችንም ኃይል ለመስጠት በሚያስችል ደረጃ የጥገና ስራ እየተጠናቀቀ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
የክልሉ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አመራርና ሰራተኞች ለወደሙ የኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማቶችን ጥገና በማድረግ ደሴ ዲስትሪክት ስር የሚገኙ አብዛኞቹ ከተሞች ኤሌክትሪክ ኃይል መልሰው አግኝተዋል፡፡
ሀርቡ ከተማን ጨምሮ ደሴ፣ ኮምቦልቻ፣ከሚሴ፣ባቲ፣ ማጀቴ፣ ጨፋ ሮቢት፣ አቀስታ፣ መሀልሳይንት፣ ሳይንት አጅባር፣መኮይ፣አልብኮ፣ መካነሰላም ፣ከላላ ፣ተንታ፣ማሻ ፣ወግዲ እና ሌሎች የሳተላይት ከተሞች ጨምሮ የኤሌክትሪክ ሃይል ማግኘታቸው ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!