አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የቦስተን ግብረ ሃይል ከቦስተን የኢትዮጵያውያን ስፖርት ክለብ ጋር በመተባበር 89 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ግምት ያላቸው 17 ቬንትሌተሮች ለጤና ሚኒስቴር ድጋፍ አድርጓል፡፡
ክለቡ በአሜሪካ ለኢትዮጵያ ኢምባሲ ያስረከቧቸው ቬንትሌተሮች ለጤና ሚኒስቴር መላካቸውን ነው አምባሳደር ፍጹም አረጋ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ያስታወቁት፡፡
አምባሳደር ፍጹም ክለቡን እና ማሽኖቹን በመመርመር እና የመጋዘንና ተያያዥ ወጪዎችን በመሸፈን አስተዋፅኦ ያደረጉ ግለሰቦችንና የኢትዮጵያ አየር መንገድን አመስግነው፥ ሌሎችም ተመሳሳይ ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

