Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የጤና ሚኒስቴር የወደሙ የጤና ተቋማትን መልሶ ለማቋቋም የድጋፍ ጥሪ አቀረበ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 6 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከፍተኛ ውድመት የደረሰባቸውን የጤና ተቋማት ለማቋቋምና መልሶ ስራ ለማስጀመር የጤና ሚኒስቴር ጥሪ አቀረበ፡፡

አሸባሪው ህወሓት በወረራ ይዟቸው በነበሩ አካባቢዎች ህዝብ የሚገለገልባቸውን የጤና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት፤ የህክምና ግብዓት ማከማቻ ተቋማትን እና ሌሎች ማህበራዊ ተቋማት ማውደሙ ተገልጿል፡፡

የህክምና መሳርያዎችን እና ሌሎች ግብዓቶችንም ጭኖ በመውሰዱ ዝርፍያ እና ጉዳት ፈጽሟል፡፡

በእስካሁኑ መረጃም ከ2 ሺህ 700 በላይ የሚሆኑ የጤና ተቋማት አገልግሎት እንደማይሰጡ ታውቋል፡፡

በጤና ተቋማቱ ላይ በተከሰተዉ መጠነ ሰፊ ወድመት ምክንያት በርካታ ዜጎች የጤና አግልግሎት የሚያገኙበት በከፊልና ሙሉ ለሙሉ ተስተጓጉሏል፤ እንዲሁም ግጭቱ በተከሰተባችዉ አካባቢዎች አቅራቢያ አገልግሎት የሚሰጡ ሆስፒታሎች እና ጤና ጣቢያዎች እንዲጨናነቁ እና መደበኛ ከሆነዉ አቅማቸዉ በላይ አገልግሎት እንዲሰጡ አስገድዷል።

በመሆኑም የጤና ሚኒስቴር ለህብረተሰቡ ቀጣይነት ያለዉ አገልግሎት ለመስጠት እንዲያስችል እና አገልግሎቱን ወደ ነበረበት ለመመለስ ሁሉን አቀፍ ጥሪ አቅርቧል፡፡

ሚኒስቴሩ የሃብት ማሰባብሰብ እና ድጋፍ ስራን ለማስተባበርም የባለሙያ ቡድን ያቋቋመ ሲሆን፥ በግለሰብም ሆነ በቡድን ድጋፍ ማድረግ ለሚፈልጉ ሁሉ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አስፈላጊ መረጃ እና ትብብር ለመስጠት ዝግጁ መሆኑንም ገልጿል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version