Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ኢንስቲትዩቱ በምርምር ያገኘውን ዘመናዊ የሰብል መፈልፈያ ማሽን አስተዋወቀ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ባዮቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ከኦሮሚያ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ባለስልጣን ጋር በመተባበር በምርምር ያገኘውን ዘመናዊ የበቆሎና ሌሎች ሰብሎች መፈልፈያ ማሽን አስተዋውቋል፡፡

ኢንስቲትዩቱ በጅማ ዞን ቀርሳ ወረዳ ማሽኑን ያስተዋወቀ ሲሆን፥ በቀጣይ በቆሎ አብቃይ በሆኑ አካባቢዎች ለማስፋፋት እንደሚሰራ አስታውቋል።

የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ካሳሁን ተስፋዬ፥ ማሽኑ መንግስት አርሶ አደሩን የግብርና ተክኖሎጂ ተጠቃሚ ለማድረግ የሚያደርደርገው አካል መሆኑን ተናግሯል።

ቴክኖሎጂውን ለመስራት አንድ አመት ተኩል እንደፈጀ የጠቆሙት ዳይሬክተሩ፥ በቆሎን ጨምሮ 7 ዓይነት ሰብሎችን መፈልፈል እንደሚችልም ገልፀዋል።

አዲሱ ቴክኖሎጂ የምርት ብክነትን ከመቀነስ አንፃር ትልቅ ፋይዳ እንዳለው ተመልክቷል፡፡

በሁሴን ከማል

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version