አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ጎንደር ዞን ደብረ ታቦር ከተማ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ተተኳሽ ጥይት ደብቃ የተገኘች ግለሰብ በቁጥጥር ስር መዋሏን ፖሊስ አስታወቀ።
የደብረ ተቦር ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ዋና ኢንስፔክተር ያለው ዘለቀ እንደገለጹት÷ ግለሰቧ በቁጥጥር ስር የዋለችው ትናንት ምሽት ሶስት ሰዓት ላይ ነው።
ፖሊስ ከህብረተሰቡ በደረሰው ጥቆማ መሰረት በከተማው ቀበሌ 02 በሚገኝ መኖሪያ ቤቷ ባደረገው ድንገተኛ ፍተሻ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የክላሽንኮቭ ጠብመንጃ ጥይት መገኘቱን ተናግረዋል።
ተጠርጣሪ ግለሰቧ በቁጥጥር ስር ውላ ምርምራ እየተደረገባት መሆኑን ነው የገለጹት።
ከጉዳዩ ጋር ግንኙነት ያላቸው ሌሎች ተጠርጣሪዎችን ለመያዝም ክትትል እየተደረገ መሆኑን ዋና ኢንስፔክተሩ መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
ህብረተሰቡ አካባቢውን ከህገ ወጥ ተግባራትና ሰርጎ ገቦች ለመጠበቅ እያደረገ ያለውን ተሳትፎ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

