አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 6 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶክተር በለጠ ሞላ በኢትዮጵያ ከፖላንድ አምባሳደር ፕሪዝሚይስላው ቦባክን ጋር ተወያዩ፡፡
በውይይቱ ሁለቱ ሀገራት በሳይንስ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ዘርፍ በጋራ መስራት በሚችሉበት ጉዳይ ዙሪያ መክረዋል።
ዶክተር በለጠ ሞላ ፖላንድ በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ዘርፍ የዳበረ ልምድ ያላት ሃገር በመሆኗ ኢትዮጵያ በዚህ ዘርፍ ከፖላንድ ልምድና ድጋፍ ማግኘት ትፈልጋለች ብለዋል።
ኢትዮጵያ የዲጂታል ኢኮኖሚን ለመገንባት እየሰራች ነው ያሉት ሚኒስትሩ ፖላንድ በተለይ በኤሌክትሮኒክስ ባንኪንግ ያላትን የዳበረ ልምድ መውሰድ እንፈልጋለን ነው ያሉት።
አምባሳደር ፕሪዝሚይስላው ቦባክን በበኩላቸው ÷ ሀገራቸው በኤሌክትሮኒክስ ባንኪንግ፣ በታክስ አስተዳደር፣ በዴታ ኢንተግሬሽን፣ በጂኦስፓሻል ኢንፎርሜሽን ሲስተም ያላትን ልምድ ለኢትዮጵያ ለማካፈል ዝግጁ መሆኗን አረጋግጠዋል።
የኢትዮጵያን የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ስራ ፖላንድ ለመደገፍ ዝግጁ ናት ያሉት አምባሳደሩ የኢትዮጵያ ባለሙያዎች በዘርፉ ልምድ የሚወስዱባቸውን እድሎችም እናመቻቻለን ብለዋል።
ሁለቱ ሀገራት የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ስራ ላይ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የትብብር ማዕቀፍ በማዘጋጀት ወደ ስራ ለመግባት ከስምምነት መድረሳቸውን ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

