አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሦስት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ለጀግናው መከላከያ ሰራዊት የ72 ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርገዋል፡፡
የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ጀማል የሱፍ ዩኒቨርሲቲው 15 ሚሊየን ብር ድጋፍ ማድረጉን ጠቅሰው፥ “አገርና ትውልድን የማስቀጠል ሃላፊነት በሚገባ በመገንዘብ ዛሬም ለጀግኖቻችን ድጋፍ በማድረጋችን ታላቅ ኩራት ተሰምቶናል” ብለዋል፡፡
የመቱ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር እንደገና አበበ በበኩላቸው፥ ዩኒቨርሲቲው 22 ሚሊየን ብር ድጋፍ ማድረጉን ተናግረዋል።
ዜጎችን በትምህርት በመቅረፅ ለቁም ነገር ማብቃት የሚቻለው አገር በተረጋጋ ሰላማዊ ሁኔታ ላይ ስትሆን በመሆኑ እኛም ለአገራችን ሰላም የድርሻችን ለመወጣት ድጋፍ አድርገናል ነው ያሉት።
ጅማ ዩኒቨርሲቲ 35 ሚሊየን ብር ድጋፍ ማድረጉን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር ጀማል አባፊጣ ገልጸዋል።
ፕሬዚዳንቱ የአገር ዋልታና ምሰሶ በመሆን የአባቶቹን የጀግንነት ታሪክ ጠብቆ የራሱን አዲስ ታሪክ እየፃፈ ለሚገኘው ጀግናው መከላከያ ሰራዊት ድጋፍ ማድረግ እድለኝነት ነው ብለዋል።
የመከላከያ ፋይናንስ ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ወይዘሮ ማርታ ሉዊ፥ አገርን ለማዳን የሚደረገውን ዘመቻ በመደገፍ በደጀንነት ለቆሙት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ምስጋና ማቅረባቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

