Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ተቀማጭነታቸውን አዲስ አበባ ካደረጉ የአፍሪካ አገራት አምባሳደሮች ጋር ውይይት ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የጎረቤት አገራትና የኢጋድ ጉዳዮች ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ፍስሀ ሻውል፣ የዓለም አቀፍ ድርጅቶች ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮሴፍ ካሳዬ ተቀማጭነታቸውን አዲስ አበባ ካደረጉ የአፍሪካ ሀገራት አምባሳደሮች ጋር ውይይት አድርገዋል።
 
የህወሓት ወራሪ ቡድን ይዟቸው በነበሩ ቦታዎች የፈጸማቸውን አሰቃቂ ጭፍጨፋና የንብረት ውድመት በተመለከተ የጎረቤት አገራትና የኢጋድ ጉዳዮች ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ፍስሀ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
 
አንዳንድ ምዕራባውያን አገራትና የመገናኛ ብዙሃን ሀሰተኛ ዘገባዎችን በማሰራጨት በህዝብ የተመረጠን መንግስት ወደ ጎን በመተው የሽብር ቡድኑን የሚደግፍና የአገሪቱና ገጽታ የማጠልሸት እንቅስቃሴን እየገፉበት እንደሆነ አምባሳደሩ ገልጸዋል።
 
የዓለም አቀፍ ድርጅቶች ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮሴፍ በበኩላቸው÷ ̍አፍሪካውያን የውስጥ ጉዳዮቻችንን በራሳችን የመፍታት አቅም ያለን በመሆናችን የውጭ ጣልቃ ገብነትን በጋራ መቃወም ይገባናል” ብለዋል።
 
በርካታ የአፍሪካ አገራት “የበቃ ዘመቻን” በመቀላቀላቸው አመስግነው ያልተቀላቀሉም እንዲቀላቀሉ ለአምባሳደሮቹ ጥሪ ማቅረባቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
 
በተወሰኑ ትርፍ የፖለቲካ ፍላጎት ባላቸው አገራት አማካኝነት በስዊዘርላንድ ጄኔቫ የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት በኢትዮጵያ ላይ የጠራው ስብሰባ ውድቅ እንዲደረግ፥ የአፍሪካ አገራት እና ወዳጅ አገራት ከኢትዮጵያ ጎን እንዲቆሙም ጥሪ ቀርቧል፡፡
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version