Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ካረን ባስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ኢትዮጵያን ከአጎዋ እንዳያግዱ እና እንድትቆይ ጥረት እያደረጉ መሆኑን አስታወቁ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 6 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካ የተወካዮች ምክር ቤት አባል የሆኑት ካረን ባስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ኢትዮጵያን ከአጎዋ እንዳያግዱ እና እንድትቆይ ጥረት እያደረጉ መሆኑን አስታወቁ።
 
በተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ የአፍሪካ ንዑስ ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑት ካረን ባስ ኢትዮጵያን በአጎዋ ስምምነት ለማቆየት የሚደረገው ጥረት ውጤት እንደሚያመጣ ተስፋ አለኝ ሲሉ ለኢትዮጵያ አሜሪካውያን የዜጎች ምክር ቤት ገልጸዋል።
ሴንተር ጂም ኢንሆፍ ለምክር ቤቱ ባደረጉት ንግግር አሜሪካ እየቀጣች ያለችው መቀጣት የማይገባቸውን ነው ብለዋል።
 
ዋሽንግተን ኢትዮጵያን ከአጎዋ በማስወጣት ለዓመታት አጋራችን የነበረችን ሀገር እየጎዳች መሆኗንም ነው ያመለከቱት።
 
ከዚያም ባለፈ መዋዕለ ንዋያቸውን በኢትዮጵያ ያፈሰሱ እና ሊያፈሱ ያሉ የአሜሪካ ኩባንያዎችንም መጎዳት እንደሆነ አስረድተዋል።
 
የፕሬዚዳንት ባይደን አስተዳደር ኢትዮጵያን ከገጎዋ በማስወጣት ፍላጎቱን ለመጫን ሲጥር ቆይቷል።
 
ሆኖም ኢትዮጵያዊያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች ሀገሪቱን ከአጎዋ ማስወጣት ከባድ ስህተት መሆኑን ሲገልፁ ቆይተዋል።
 
ውሳኔው የተሳሳተ መረጃን መሠረት ያደረገ ከመሆኑ ባለፈ ኢትዮጵያ ከአጎዋ ብትወጣ በዋናነት የሚጎዳው በ10 ሺህዎች የሚቆጠሩ የፋብሪካ ሰራተኞች መሆናቸውንም ያነሳሉ።
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version