አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው ህወሓት በወረራ ይዟቸው በነበሩ የአማራና የአፋር ክልሎች ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን ሄክታር በላይ የእርሻ መሬት ከልማት ውጭ ማድረጉን ግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ።
በዘንድሮ መኸር 13 ሚሊየን ሄክታር መሬት በማረስ 375 ሚሊየን ኩንታል ምርት ለማግኘት ታቅዶ ወደ ስራ መገባቱን የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር መለስ መኮንን ገልጸዋል፡፡
ይሁን እንጂ የሽብር ቡድኑ በወረራ ይዟቸው በነበሩት የአማራና የአፋር ክልሎች ከሚገኝ ለመኸር እርሻ የሚውል ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን ሄክታር በሚልቅ በዘር የተሸፈነ መሬት፣ ለምርት የደረሰ እና በማደግ ላይ የነበረን ሰብል ሙሉ በሙሉ ከጥቅም ውጭ አድርጓል ብለዋል።
አሸባሪ ቡድኑ የአርሶ አደሩን መሬት በታንክና በመኪና ሄዶባቸዋል፣ የእርሻ መሬቱን የጅምላ መቃብር አድርጎታል ገሚሱንም ምሽግ ሰርቶበታል ነው ያሉት።
የሽብር ቡድኑ የአርሶ አደሩን የእርሻ መሳሪያዎች ዘርፏል፤ ለእርሻ የሚጠቀምባቸውን በሬዎቹን አርዶ በልቶበታል፤ ነድቶ ወስዶበታል እንዲሁም ገድሎበታል ሲሉ ነው የተናገሩት።
በተጨማሪም በአካባቢዎቹ የሚገኙ አርሶ አደሮች ተረጋግተው እንዳያርሱ፣ ምርታቸውን እንዳይንከባከቡና በስጋት እንዲቆዩ ማድረጉንም ሚኒስትር ዴኤታው ጠቅሰዋል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

