Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በአዲስ አበባ የሚገኙ የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆች ለሀገር መከላከያ ሰራዊት የአይነት ድጋፍ አስረከቡ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 7 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ቴክኒክ ሙያ ስልጠና እና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ስር የሚገኙ የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆች ከ23 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ስንቅና ቁሳቁስ ለሀገር መከላከያ ሰራዊት አስረከቡ።
ድጋፉን በደሴ ግንባር በመገኘት ማስረከባቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፕሬስ ሴክሬታሪያት መረጃ ያመላክታል።
ድጋፉ የተሰበሰበው በቢሮው ስር ከሚገኙ አመራሮችና ሰራተኞች፣ የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆች እና የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጅ ተቋማት ነው።
ከዚህ ቀደም 47 የቢሮው አመራሮችና ፈፃሚዎች ወደ ግንባር መዝመታቸዉ ይታወሳል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version