Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ለተመድ የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት ግልጽ ደብዳቤ ፃፈ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 7 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ለተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ናዛት ካን፣ ለሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት አባላት እንዲሁም ለተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ሚሼል ባቼሌት ግልጽ ደብዳቤ ፃፈ።

የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በጻፈው ደብዳቤ፥ በሰሜን የሀገሪቱ ክፍል እስከ ፈረንጆቹ ሕዳር 3 ቀን 2021ድረስ የተፈጸሙትን የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች በሌላ አካል በድጋሚ እንዲጣራ ማድረግ በተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት እና በኢትጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በጥምረት የተካሄደውን ምርመራ እውቅና መንፈግ ነው ብሏል፡፡

ኮሚሽኑ ምርመራ ተደርጎ በሪፖርት የቀረበውን ጉዳት በሌላ አካል ከማስደገምና ሂደቱን ከማጓተት፣ ቀደም ብሎ በወጣው የምርመራ ሪፖርት መሰረት ተጎጂዎች እንዲያገግሙ፣ ወደ ተፈናቀሉበት ቦታ እንዲመለሱ እንዲሁም እንዲካሱ ብሎም ወንጀል የፈጸሙ አካላት ተጠያቂ እንዲሆኑ መሠራት ነበረበትም ብሏል በደብዳቤው፡፡

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በደብዳቤው  የሰብዓዊ መብት ጥሰቱ እንደገና ይጣራ ከተባለ አጥፊዎቹ አካላት የፈጸሙትን የሰብዓዊ መብት ጥሰት ለመካድና እና ኮሚሽኑ የሰራውን ምርመራ ለማጣጣል እድል ከመስጠቱም ባሻገር የኮሚሽኑን ተግባር ዝቅ የሚያደርግ ይሆናል ማለቱንም ከውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል ።

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version