Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ደቡብ ሱዳን ከኢትዮጵያ ጎን እንደምትቆም አረጋገጡ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 7 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ሱዳኑ ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ማያርዲት ደቡብ ሱዳን ከኢትዮጵያ ጎን እንደምትቆም አረጋገጡ።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከደቡብ ሱዳኑ ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ማያርዲት ጋር በዛሬው እለት በሁለትዮሽና የጋራ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል።

በዚህ ወቅትም ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ሀገራቸው የኢትዮጵያን ሰላም፣ መረጋጋት፣ ደህንነት እና የግዛት አንድነት ለማስጠበቅ ሁልጊዜም ከኢትዮጵያ ጎን እንደምትቆም አረጋግጠዋል።

ጁባ በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ላይ የሚደረግን ጣልቃ ገብነት አትቅበልም ያሉት ፕሬዚዳንት ኪር፥ ኢትዮጵያ የውስጥ ችግሮቿን በራሷ የመፍታት አቅም እንዳላት ያላቸውን እምነትም ገልጸዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በበኩላቸው፥ በህወሓት አማካኝነት ስለተጀመረው ግጭት እና የተወሰደውን የህግ ማስከበር ዘመቻ በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ከዚህ ባለፈም በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል ስላለው ሁኔታ እና በግጭቱ ለተጎዱ ወገኖች እየተደረገ ስላለው ሰብአዊ ድጋፍም ለፕሬዚዳንቱ ማብራሪያና ገለጻ አድርገውላቸዋል።

አያይዘውም አሁን ላይ የኢትዮጵያ ጥምር ሃይል እያስመዘገበ ባለው ድል መሬት ላይ ያለው እውነታ እየተቀየረ መሆኑንም በማብራሪያቸው አንስተዋል።

ከዚህ ባለፈም በኢትዮጵያ ሰላምን ለማስፈን በማሰብ ለማድረግ በታቀደው ሁሉን አቀፍ – አካታች ውይይት ዙሪያ ማብራሪያ መስጠታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version