Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በሚኒባሶች እና ታክሲዎች ላይ ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ የታሪፍ ማሻሻያ ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳሰ 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በመዲናዋ በሚኒባሶች እና ታክሲዎች ላይ ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ የታሪፍ ማሻሻያ ይፋ ሆነ፡፡
 
የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ የታሪፍ ማሻሻያን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል፡፡
 
በዚህ መሰረትም በሚኒባስ (ቅጥቅጥ ወይም ሃይገር ባስ) የተደረገው የታሪፍ ማሻሻያ በሚኒባስ በኪሎሜትር ከ40 ሳንቲም ወደ 45 ሳንቲም ከፍ የተደረገ ሲሆን÷ በታክሲ ደግሞ በኪሎሜትር ከ90 ሳንቲም ወደ 1ብር ከፍ ብሏል፡፡
 
በሚኒባሶች የተደረገው ጭማሪ ዝቅተኛው 1 ብር ሲሆን÷ ከፍተኛው ደግሞ 2 ብር ሆኗል፡፡
 
በታክሲ ላይ የተደረገው ጭማሪ ዝቅተኛ 50 ሳንቲም ሲሆን ÷ከፍተኛው ጭማሪ 3 ብር ከ50 ሳንቲም መሆኑ ተገልጿል፡፡
 
ጭማሪው የኪሎሜትር ርቀትን ታሳቢ ያደረገ መሆኑ በመግለጫው ተመላክቷል፡፡
 
የታሪፍ ጭማሪው በብዙሃን ትራንስፖርት ላይ እንዳልተደረገ የከተማው የትራንስፖርት ቢሮ ዛሬ በመግለጫው አሳውቋል፡፡
 
በታሪኩ ለገሰ
Exit mobile version