አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽህፈት ቤት አመራሮች በሀገር ህልውና ማስከበር ዘመቻ ላይ እየተሳተፉ ለሚገኙ የዘማች ቤተሰቦች በዛሬው ዕለት ድጋፍ አድርገዋል፡፡
አመራሮቹ በአዲስ አበባ ከሁሉም ክፍለ ከተሞች ለተውጣጡ 220 የዘማች ቤተሰቦች ነው ለእያንዳንዳቸው 50 ኪሎ ግራም ፍርኖ ዱቄትና 5 ሊትር ዘይት ድጋፍ ያደረጉት፡፡
የብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽህፈት ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ምክትል ሃላፊ አቶ ካሊድ አልዋን÷ ከጀግኖች ዘማች ቤተሰቦች ጋር በመሆን የፓርቲዬን አጋርነት ስገልጽ ከፍተኛ ክብር ይሰማኛል ብለዋል፡፡
የጀግኖች ቤተሰቦች በዘማቾች የተነሳ ሊደርስባቸው የሚችለውን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጫና ሁሉም ኢትዮጵያዊ ማቃለል እንዳለበትም አሳስበዋል፡፡
አቶ ካሊድ ብልጽግና ፓርቲ በዚህ ረገድ ያለበትን ሃላፊነት በብቃት ለመወጣት ዝግጁነቱን አሳይቷል ማለታቸውን ከብልጽግና ፓርቲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ሀገር ለማፍረስ የተነሳውን ጠላት ሁሉም ኢትዮጵያውያን በተለያዩ ዘርፎች በመሰማራት እየተዋጉት ነው ያሉት ሃላፊው ÷ብልጽግና ፓርቲም የዘመቻ ግንባሮች የመሪነት ሚናውን እየተወጣ መሆኑን አብራርተዋል፡፡
የብልጽግና ፓርቲ አመራሮችና ሰራተኞች ባለፈው ሳምንትም በበራኽ ወረዳ በመገኘት የዘማች ቤተሰቦችን ሰብል መሰብሰባቸው ይታወሳል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

