አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጠቅላይ ሚኒስትሩን ጥሪ ተቀብለው ወደ ኢትዮጵያ እየገቡ መሆናቸውን ዳያስፖራዎች ገለጹ፡፡
ዳያስፖራዎቹ ወደ ኢትዮጵያ የመጡት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን እንዲሁም ወዳጆቿ ያደረጉትን ጥሪ ተቀብለው ነው።
ወደ አገር ቤት ከመጡት ውስጥ ለኢትዮጵያ ክብርና ሉአላዊነት እየተፋለመ ለሚገኘው የመከላከያ ሰራዊት መድሃኒቶችን የያዙም ይገኙበታል።
“ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባቀረቡልን ጥሪ መሰረት ወደ አገር ቤት የገባነውም ለግል ወይም ለቤተሰብ ጉዳይ ሳይሆን ለአገር ጥሪ ምላሽ ለመስጠት በመሆኑ የመጣንበትን ዓላማ ለማሳካት መዘጋጀት አለብን” ነው ያሉት።
አሸባሪው ህወሓት ኢትዮጵያን ይመራ በነበረበት ወቅት በነበረው አምባገነናዊ ስርዓት ተማረው ከአገር የወጡ የዳያስፖራ አባላትም ይግኙበታል።
የዳያስፖራ አባላቱ አንዳንድ የምዕራባውያን አገራት በህዝብ ትግል ከስልጣን የተባረረውን አሸባሪ ቡድን ዳግም ወደ ስልጣን ለመመለስ የሚያደርጉትን ሴራ አጥብቀው እንደሚቃወሙ ገልጸዋል፡፡
ከዚህ አኳያ ለኢትዮጵያ ህልውና መጠበቅ ዘብ ለሆነው የመከላከያ ሰራዊት በሙያ እገዛ ከማድረግ ጀምሮ የሚጠበቅባቸውን ሁሉ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን ነው የተናገሩት፡፡
ዳያስፖራው ወደ ሀገሩ ሲመጣ ለሀገር ጠቀሜታ ያላቸውን ነገሮች ይዞ በመምጣት አለኝታነቱን በተግባር እንዲያሳይ ጥሪ ማቅረባቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

