Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ኢትዮጵያ ከምንጊዜውም በላይ የህዝቧን አንድ መሆን እና ተባብሮ መስራትን የምትፈልግበት ጊዜ ላይ ናት – ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 8 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አንጎላ የተገኙት ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ በአንጎላ ከሚኖሩ የኢትዮጵያ ማህበረሰብ አባላት ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡

ኢትዮጵያ ከምንጊዜውም በላይ የህዝቧን አንድ መሆን እና ተባብሮ መስራትን የምትፈልግበት ጊዜ ላይ ናት ያሉት ፕሬዚዳንቷ ኢትዮጵያውያኑ አንድነታቸውን እንዲያጠናክሩ ጠይቀዋል፡፡

በአንጎላ የሚኖሩት ኢትዮጵያውያን በበኩላቸው÷ በኮቪድ ወረርሺኝ ወቅትም ሆነ ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ድጋፍ በተጠየቁበት ጊዜ ሁሉ አስፈላጊውን ድጋፍ ሲያደርጉ ስለመቆየታቸው ገልፀዋል፡፡

በጦርነቱ ምክንያት ከደረሰው ውድመት ለማገገም በሚደረገው ጥረትም የሚችሉትን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን ማረጋገጣቸውን ኢቢሲ ዘግቧል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ በአንጎላ የሚኖሩት ኢትዮጵያውያን ለዳያስፖራው የተከፈቱ እንደ “አይዞን” ያሉ የድጋፍ አማራጮችን እንዲጠቀሙ ጠቁመዋል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version