አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 8 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ የተመድ ሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት ውሳኔን እንደማትቀበል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።
ዛሬ በኢትዮጵያ ላይ ልዩ ስብሰባ ያደረገውን ምክር ቤት ሀገራት ለራሳቸው ፖለቲካዊ አጀንዳ ማስፈፀሚያ እየተጠቀሙት እንደሆነ ሚኒስቴሩ አስታውቋል።
ምክር ቤቱ ለተወሰኑ ሀገራት ፖለቲካዊ አጀንዳ ማስፈጸሚያነት መዋሉም እንዳሳዘነው ገልጿል።
መንግስት ምክር ቤቱ ልዩ ስብሰባ ከሚጠራ ይልቅ ገንቢና አወንታዊ በሆነ መንገድ እንዲሰራ መጠየቁን አስታውሷል።
ይሁን እንጅ ምክር ቤቱ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ተፈጽሟል ከተባለው የሰብአዊ መብት ጥሰት ጋር በተያያዘ የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት ፕሬዚዳንት እና የምክር ቤቱ አባላት እንዲተግብሩት ካስቀመጠው ምክር ሃሳብ በተቃራኒ የተፈጸመ መሆኑን አንስቷል።
በአንዳንድ አባል ሀገራት መካከል የተደረገው ይህ ድርጊትም በሀገሪቱ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ለመግባት የተወሰደ አማራጭና ሁኔታዎችን ከማማበስ ያለፈ ፋይዳ የሌለው እንደሆነም አጽንኦት ሰጥቷል።
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!