አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የፍትህ ሚኒስቴር እና ማህበራት በአፋር ክልል በአሸባሪው ህወሓት ወረራ ወቅት ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች የሚውል 3 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር እና የዓይነት ድጋፍ ዛሬ በሰመራ በመገኘት ለክልሉ ርዕሰ መሰተዳድር አቶ አወል አርባ አስረክበዋል።
ድጋፉን በጋራ ያደረጉት የፍትህ ሚኒስቴር፣ ዐቃቢያነ ህግና ሰራተኞች፣ የፌዴራል ጠበቆች ማህበር እና የኢትዮጵያ የህግ ባለሙያዎች ማህበር መሆናቸው ተገልጿል።
ድጋፉንም የፍትህ ሚኒስትሩ ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ ለአፋር ክልል ርዐሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባ ባስረከቡበት ወቅት እንደገለፁት፥ የክልሉን መንግስት እና ማህበረሰብ ለመደገፍ ዝግጁ መሆናቸውን እና በቀጣይም በሚደረገው መልሶ የማቋቋም ስራ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል።
በተያያዘ ዜናም የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ከ1ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የምግብና የንጽህና መጠበቂያ ያካተተ የዓይነት ድጋፍ በአፋር ክልል በወራሪው ቡድን ለተፈናቀሉ እና ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች የሚውል ሰብዓዊ ድጋፍ አድርጓል።
የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባ በአሸባሪው ህውሓት በክልሉ ጉዳት ለደረሰባቸው፣ ለተፈናቀሉ እና ሰብዓዊ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች አለኝታነታቸውን በማሳየታቸውም አመስግነዋል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

