Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ሀገራችን ያጋጠማትን ችግር ያለማንም ጣልቃ ገብነት እኛው እየፈታን እንገኛለን-ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሀገራችን ያጋጠማትን ችግር ያለማንም ጣልቃ ገብነት እኛው አንድ በመሆን መፍታት እንችላለን፤ እየፈታንም እንገኛለን ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናገሩ፡፡

“እኔ የእህቴ ጠባቂ ነኝ፣ ሰላም ይስፈን፣ በሴቶች እና ህፃናት ላይ የሚደርስ ጥቃት ይቁም” በሚል መሪ ቃል አሸባሪው ህወሓት በሴቶች እና ህጻናት ላይ የፈጸመውን ጥቃትና አስገድዶ መድፈር የሚያወግዝ ሰልፍ በመስቀል አደባባይ ተካሄደ።

በሰልፉ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ፥ በሀገራችን የተፈጠረውን ችግር ያለማንም ጣልቃ ገብነት እኛው አንድ በመሆን መፍታት እንችላለን፤ እየፈታንም እንገኛለን ብለዋል፡፡

ጣልቃ መግባቱ ይቁም፤ በተለይም በግጭት ሁሌም ቢሆን ሴቶች እና ህፃናት ተጠቂ በመሆናቸው ይህ እስከመጨረሻው እንዲቆም በቃ እንላለን ብለዋል።

የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ ፥ ኢትዮጵያ በሴቶች ትመሰላለች ያሉ ሲሆን ፥ ሀገራችንን ለመከፋፈል እና ለማፍረስ የተነሱ ከውጭም ከውስጥም ያሉ ሀይሎችን እንደሴትነታችን በቃ እንላለን ብለዋል ።

“እኔ ለሀገሬ ጠባቂ ነኝ “በሚለው ዘመቻም በኢትዮጵያ በተፈጠረው ግጭት ምክንያት ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ እና ጉዳት ለደረሰባቸው ሴቶችና ህፃናት ከ2 ቢሊየን ብር በላይ የሚደርስ ሀብት መሰብሰብ መቻሉን ተናግረዋል፡፡

በቅድስት ተስፋዬ

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version