Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በመቆም ለቀጣናው ሀገራት ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ የሚያደርገውን ጥረት መደገፍ አለብን -የአሜሪካ ኮንግረስ አባሏ ሼይላ ጃክሰን ሊ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከከፋፋይ ኃይሎች በተቃራኒው ተሰልፈን ከኢትዮጵያ ጋር በመቆም አሁን ያለው መንግሥት ለሀገሪቱ ሕዝቦች እና ለቀጣናው ሀገራት ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ የሚያደርገውን ጥረት መደገፍ ይገባል ሲሉ የአሜሪካ ኮንግረስ አባሏ ሼይላ ጃክሰን ሊ ገለጹ።

ኢትዮጵያ በአፍሪካ አህጉር ጠንካራ የኢኮኖሚ ሞተር ነች ያሉት የኮንግረስ አባሏ፥ በከፋፋይ ሃይሎች ሴራ ሳንዘናጋ ከኢትዮጵያ ጋር በመቆም መንግስት ለሀገሪቱ ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ የሚያደርገውን ጥረት መደገፍ አለብን ብለዋል በቲዊተር ገጻቸው ላይ።

በአፍሪካ አጎዋን ለመመሥረት በተደረገው የመጀመሪያው የመክፈቻ ጉዞ ከኮንግሬስ ልዑካን ጋር ወደ አፍሪካ መጓዛቸውን ያስታወሱት ሼይላ ጃክሰን፥ አጎዋ በዩናይትድ ስቴትስ ኮንግረስን እንዲጸድቅ አንድዋ ምክንያት ኢትዮጵያ እንደነበረችም ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል፡፡

ኢትዮጵያ በአፍሪካ ኢኮኖሚ እድገት የድርሻዋን ተሳትፎ እንድታደርግም የአጎዋ እድል ተጠቃሚነቷ መቀጠል አለበት ነዉ ያሉት።

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version