አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መርማሪ ቦርድ በሲዳማ ክልል በተለያዩ ወረዳዎችና ክፍለ ከተሞች በአዋጁ አፈጻፀም ዙሪያ የመስክ ምልከታ አካሄደ፡፡
ቦርዱ በሀዋሳ ሀይቅ ዳርና በመሀል ክፍለ ከተሞች፣ በሸበዲኖ ወረዳ ለኩ ከተማ እና በዳሌ ወረዳ ይርጋለም ከተማ ፖሊስ ጽ/ቤቶች በመገኘት የአዋጁን አፈጻፀምና የተጠርጣሪዎችን ሰብዓዊ አያያዝ ተመልክቷል፡፡
የቦርዱ ሰብሳቢ አቶ ለማ ተሰማ ÷ የቦርዱን ምልከታ ዓላማ እና አዋጁን ተላልፈዋል በሚል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉ ሰዎች መገኛ ቦታ ልየታ መደረጉን በምልከታው ወቅት አስረድተዋል፡፡
በምልከታውም በየደረጃው ከሚገኙ የፀጥታ ዘርፍ ኃላፊዎች እና አዋጁን ተላልፈዋል በሚል ከተጠረጠሩት ሰዎች ጋርም በሰብዓዊ መብት አያያዝ፣ በምግብ፣ መጠጥና በንፅህና ቁሳቁሶች አቅርቦት ዙሪያ ላይ በተናጠል
በየምልከታዎቹ ማብቂያም በየደረጃው ላሉ የጸጥታ ዘርፍ ኃላፊዎችም መልካም ጎኖችንና መሻሻል ያለባቸውን ሀሳቦች በመለየት ግብረ መልስ የሰጠ ሲሆን፥ ኃላፊዎቹም ግብረ መልሱን በመቀበል በግብረ መልሱ መሰረት የሚሰሩ መሆኑን ነው የገለፁት፡፡
ከምልከታው በኋላም ቦርዱ ለክልሉ ያዘጋጀውን የማጠቃለያ ግብረ መልስ አቅርቧል፡፡
ግብረ-መልሱን ያቀረቡት የቦርዱ ሰብሰቢ አቶ ለማ ተሰማ ፥ በሁለቱም ወረዳዎችና ክፍለ ከተሞች በሰብዓዊ አያያዝ ዙሪያ ቅሬታ አለመነሳቱን፣ ለተጠርጣሪዎች የውሀ፣ የምግብና የመፀዳጃ አገልግሎት መኖሩን፣ በቤተሰቦቻቸው እንዲጠየቁ እየተደረገ መሆኑን በጥንካሬ አንስተዋል፡፡
በቀጣይም ቦርዱ የምርመራው ሂደት ተፋጥኖ ጥፋተኛና ጥፋተኛ ያልሆነው ቢለይ የተሻለ መሆኑን በምክረ ሀሳቡ አመልክቷል፡፡
በክልሉ በሚነሱ አንዳንድ ቅሬታዎች ላይ ተገቢውን የማጣራት ስራ መስራት እንደሚያስፈልግም ነው ቦርዱ የጠቆመው፡፡
የሲዳማ ክልላዊ መንግስት የሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ አለማየሁ ጢሞቲዮስ፥ ቦርዱ በአዋጁ አፈፃጸም ዙሪያ በክልሉ ላደረገው ምልከታ አመስግነዋል፡፡
ጥቆማዎችንና ግብረ መልሶችን በመቀበልም በቀጣይ ተገቢው የማጣራት እና የማስተካከያ ስራ እንደሚሰራ ሃላፊው መግለጻቸውን ከምክርቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

