አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የትምህርት ሚኒስቴር እና የሠመራ ዩኒቨርሲቲ የትምህርት ሥርዓትን ማሻሻል በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ውይይት አካሄዱ፡፡
በኢትዮጵያ ያለው የትምህርት ስርዓት ያለበትን ደረጃ የሚያሳይ ውይይት በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች እያተከናወነ ሲሆን÷ በሰመራ ዩኒቨርሲቲ የተደረገው ውይይትም 4ኛው መድረክ መሆኑን የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ ገልፀዋል፡፡
የትምህርት ሥርዓቱ ምን መምሰል እንዳለበት ከ47 የመንግስት እና የግል ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንቶች ጋር መወያየታቸውንም ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡
የሠመራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር መሀመድ ዑስማን፥ ለሀገሪቱ የትምህርት ስርዓት መሻሻል የሚያመጡ ማናቸውም ተግባራት እንደሚከውኑ አብራርተዋል፡፡
ሚኒስቴሩም የሀገሪቱን የትምህርት ስርአት በማሻሻል የሚታሰበውን እድገት ማስመዝገብ የሚችል ምሁራንን ማፍራት እንዲቻል መስራት ይገባል ማለታቸውን ከሰመራ ዩኒቨርሲቲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
በሌላ በኩል የትምህርት ሚኒስቴር በአፋር ክልል በአሸባሪው ህወሓት የወደሙ ትምህርት ቤቶችን የጎበኘ ሲሆን÷ በፍጥነት የመልሶ ማቋቋም ግንባታ እንዲደረግ ከአካባቢው ባለድርሻ አካላት ጋር ተወያይቷል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

