Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ኢትዮጵያውያን እያደረጉት ያለው ድጋፍ ጉዳት የደረሰበት ሕዝባችንን ለማቋቋም የሚያስችል ነው-ዶ/ር ይልቃል ከፋለ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) “መላ ኢትዮጵያውያን እያደረጉት ያለው ሁለንተናዊ ድጋፍ በአሸባሪው ህወሓት ወረራ ጉዳት የደረሰበት ህዝባችንን ለማቋቋም የሚያስችል ነው” ሲሉ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ ገለጹ።

የፍትህ ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ጠበቆችና የሕግ ባለሙያዎች ማህበር ጋር በመተባበር የ3 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር እና የአይነት ድጋፍ ለአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት አስረክበዋል።

ርዕሰ መስተዳደር ዶክተር ይልቃል ከፋለ በርክክብ ስነ ስርዓቱ ላይ እንዳሉት “ ወራሪው ቡድን በህዝባችን ላይ ያደረሰው ጉዳት ከፍተኛ ቢሆንም ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን እያደረጉት ያለው ድጋፍ ተጎጂዎች የደረሰባቸውን የልብ ስብራት ለመጠገን የሚያስችል ነው ” ብለዋል።

“የፍትህ ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያዎችና የጠበቆች ማህበር ዛሬ ያደረጋችሁት ድጋፍም ለወገናችሁ ያላችሁ አጋርነት ማረጋገጫ ነው” ሲሉም ዶክተር ይልቃል ገልጸዋል።

የፍትህ ሚኒስቴር የጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ፍቃዱ ፀጋ በበኩላቸው “አሸባሪ ቡድኑ ያደረሰው መጠነ ሰፊ ጉዳትና ውድመት በአንድ ጊዜ አስተዋጽኦ ሊፈታ አይችልም” ብለዋል።

“በመሆኑም መንግሥት፣ መላ ኢትዮጵያዊያን እና ረጂ ድርጅቶች የመልሶ ማቋቋምና ግንባታ ሥራውን ለማሳካት በቀጣይ በጋራ ተረባርበን ልንሰራ ይገባል ሲሉ” መግለፃቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version