Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ዩኒሴፍ በሴቶች፣ ህጻናትና ማህበራዊ ዘርፎች የሚከናወኑ ተግባራትን ለማጠናከር ያለውን ቁርጠኝነት አረጋገጠ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ዩኒሴፍ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በሴቶች፣ ህጻናት እና ማህበራዊ ዘርፎች የሚያደርጋቸውን ሁለንተናዊ እንቅስቃሴዎች ለማጠናከር ያለውን ቁርጠኝነት ማረጋገጡን በኢትዮጵያ የዩኒሴፍ ጊዜያዊ ተወካይ ጂያንፍራንኮ ሮቲጅሊያኖ በኩል አስታወቀ፡፡
የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ ከጂያንፍራንኮ ሮቲጅሊያኖ ጋር በነበራቸው ውይይት÷ በሀገሪቱ ግጭት በተፈጠረባቸው አካባቢዎች ተፈናቃይ ዜጎችን ለመደገፍ በትኩረት ሲሰራ መቆየቱን አብራርተዋል።
ሚኒስቴሩ ለተፈናቃዮች ማህበራዊ አገልግሎት ለማድረስ እያደረገ ያለውን ጥረት እንዲሁም የሴቶችና ወጣቶችን የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየሰራ ያለውን ስራ በተመለከ ማብራሪያ ሰጥተረዋል።
በውይይቱ ወቅት ዩኒሴፍ በሴቶችና ወጣቶች ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ላይ በሚያደርገው ድጋፍ ላይ መምከራቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል።
በኢትዮጵያ የዩኒሴፍ ጊዜያዊ ተወካይ ጂያንፍራንኮ ሮቲጅሊያኖ በበኩላቸው÷ ኢትዮጵያ ከዩኒሴፍ ጋር በትብብር የሰራችው ስራ የህጻናትን ችግር ለመቅረፍ ማስቻሉን ጠቅሰዋል።
ዩኒሴፍ ሚኒስቴሩን በመረጃ ስርአት ግንባታ፣ የወጣቶች መረጃን ዲጂታላይዝድ በማድረግ፣ በአገር አቀፍና በክልል ደረጃ ሰፊ የአቅም ግንባታ ስራዎችን ለመደገፍ ዝግጁ መሆኑንም አረጋግጠዋል፡፡
ዶክተር ኤርጎጌ ዩኒሴፍ ከኢትዮጵያ ጋር የሚያደርገውን ያልተቆጠበ ድጋፍና አጋርነት አድንቀው የጋራ አላማችንን ከግብ ለማድረስ የሚያደርገውን ከፍተኛ የቴክኒክ እና የገንዘብ ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version