Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የሽብር ቡድኑን ህወሓት ሲፋለም ለተሰዋው ጀግናው መቶ አለቃ ጌታቸው ሞረዳ ልጅ የቤት ስጦታ ተበረከተለት

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳድር የሽብር ቡድኑን ህወሓት ሲፋለም ለተሰዋው የሀገር መከላከያ ሰራዊት አባሉ ጀግናው መቶ አለቃ ጌታቸው ሞረዳ ልጅ በህገወጥ መንገድ ተይዘው ከተገኙ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ውስጥ አንዱን በስጦታ አብርክቷል፡፡
 
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳድር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ እንዳስታወቁ፥ህይወታቸውን ለአገራቸው ሲሉ ለሰው የሰራዊቱ አባል ቤተሰቦች አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ የቅድመ ዝግጅት ተግባራት እየተከናወነ ይገኛል፡፡
 
ለ40 ቀን በአባቱ እቅፍ ውስጥ ሆኖ ለኢትዮጵያ የተዋጋውን ህፃን ቢኒያም ጌታቸውን እና አሳዳጊ አክስቶቹን ዛሬ በአካል ማግኘታቸውንም ገልጸዋል፡፡
 
የጀግናው መቶ አለቃ ጌታቸው ሞረዳ ልጅ በእዚህ የጨቅላነት ዕድሜው ማየት የማይገባውን አይቷል፤ የኢትዮጵያ ጀግኖች ልጆች ለአገራቸው ሲዋደቁ በልጅነት አይኑ፣ በህፃን አእምሮው ቀርፆ አስቀምጧል ነው ያሉት።
 
ለቢኒያም አሳዳጊዎች በ2013 ዓመተ ምህረት በተጣራው መሰረት በህገወጥ መንገድ ተይዘው ከተገኙ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ውስጥ አንዱን ማበርከታቸውንም ተናግረዋል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version