Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

አሸባሪው ህወሓት የፈጸማቸውን የወንጀል ድርጊቶች የሚያጣሩ 11 መርማሪ ቡድኖች ተሰማርተዋል

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 12 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራና አፋር ክልሎች አሸባሪው ህወሓት የፈጸማቸውን የወንጀል ድርጊቶች የሚያጣሩ 11 መርማሪ ቡድኖች መሰማራታቸውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መምሪያ ዕዝ አባል የሆነው የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።
 
የፌዴራል ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር ጀነራልና የወንጀል ምርመራ ቢሮ ኃላፊ ዘላለም መንግሥቴ እንደገለጹት÷ አሸባሪ ቡድኑ በአማራና አፋር ክልሎች የፈጸመው ኢሰብዓዊ ድርጊቶች በወንጀል የሚያስጠይቁት ናቸው።
 
በአሁኑ ወቅት በጠቅላይ ሚኒስትሩ አመራር ሰጪነት የወገን ሃይል ወንጀል ፈጻሚውን አሸባሪ ቡድን መመከት መቻሉን ተናግረዋል።
 
አሸባሪው ህወሓት በገባባቸው አካባቢዎች የፈጸማቸውን ኢ-ሰብዓዊ ድርጊቶች ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብና ለኢትዮጵያ ሕዝብ ለማጋለጥ እንቅስቃሴ መጀመሩን ኮሚሽነር ጄኔራል ዘላለም አስረድተዋል።
 
ቢሮው ከፍትህ ሚኒስቴርና ከክልሎቹ ፖሊስ ጋር የተቀናጀ ኮማንድ በማደራጀትና የሥራ መመሪያ በመስጠት ማሰማራቱን ነው ያስታወቁት።
 
ቡድኖቹ በአማራ ክልል በሰሜን ሸዋ፣ ኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ እንዲሁም በአፋር ክልል በጭፍራና ካሳጊታ መግባታቸውን አስረድተዋል።
 
በአሸባሪው ህወሓት የተገደሉ፣ የተደፈሩ፣ የተጨፈጨፉና ግፍ የተፈጸመባቸው ንጹሃን ዜጎች ጉዳይ በዓለም አቀፍ ደረጃ ጭምር እንዲጠየቅ ይደረጋል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
 
የምርመራ ቡድኑ የደረሰበት ውጤትም በእንግሊዝኛ፣ ፈረንሳይኛና ሌሎች የዓለም አቀፍ ቋንቋዎች ተተርጉሞ ለዓለም ህዝብ ይፋ እንደሚሆን ምክትል ኮሚሽነር ጄነራል ዘላለም ገልጸዋል።

 

የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ በበኩላቸው÷ ጦርነቱ በታሪክ ተሸንፈው የማያውቁት ኢትዮጵያውያን ሀገርን ለማፍረስ ከተነሱ ታሪካዊ ጠላቶችና ተላላኪዎቻቸው ጋር እንደሆነ አስረድተዋል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version