አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 13 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሸባሪው ህወሃት ወታደሮች በዘረፉት እና በአወደሙት ሆስፒታል ቁስለኛ ሆነው ታክመውበታል፡፡
በጋሸና ግንባር የዓፄ ውሃ ምሽግ በጀግናው መከላከያ ሰራዊት በአማራ ልዩ ሐይል፣ ፋኖ እና ሚሊሻ ሲደመሰስ
የሽብር ቡድኑ ለውጊያ ያዘጋጃቸው ታጣቂዎቹ ሙት እና ቁስለኛ ሆነዋል።
በነበረው ውጊያ አርቢት በሚባለው አካባቢ የቆሰሉ የጁንታው ወታደሮች በየመንገዱ ወድቀው የተመለከቱ አርሶ አደሮች ቁስለኞችን በማንሳት ለመከላከያ ሰራዊቱ አስረክበዋል።
የመከላከያ ሰራዊቱም ቁስለኞችን በመንከባከብ በነፋስ መውጫ ሆስፒታል አስፈላጊውን ህክምና ሲያደርግላቸው ቆይቷል።
ቀድሞውንም የሽብር ቡድኑ የነፋስ መውጫ ሆስፒታልን ዘርፎና አውድሞት ስለነበር እነዚህ ወታደሮች ባወደሙት ሆስፒታል እንደገና ሊታከሙበት ችለዋል።
ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ያነጋገራቸው የጁንታው ቁስለኞች በአርሶ አደሮቹ እና በነፋስ መውጫ ሆስፒታል የጤና ባለሙያዎች ለተደረገላቸው ክብካቤ አመስግነዋል።
የሽብር ቡድኑ በየአውደ ውጊያው ያሰለፋቸው የትግራይ ወጣቶች እንደ ቅጠል ረግፈው ቀርተዋል የሚሉት ቁስለኞቹ፥ እኛ በአማራ ህዝብ ችርነት ለዚህ መብቃታችን አስደስቶናል ብለዋል።
በህዝቡ ላይ የደረሰው ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ውድመት በእጅጉ እንዳሳዘናቸውም ነው የተናገሩት።
በምንይችል አዘዘው
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

