አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 13 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በህወሃት ሽብር ቡድን በ4 ዓመት ልጇ ፊት በቡድን የተደፈረችውና የአምስት ወር ጽንሷ የተቋረጠባት የ27 ዓመቷ የሸዋሮቢት ከተማ ወጣት ለከፋ የጤናና ስነ ልቦና ችግር ተጋልጣለች።
የሽብር ቡድኑ በሸዋሮቢት ከተማ ሀብትና ንብረት ከማውደምና ከመዝረፉ ባሻገር በሴቶችና ህጻናት ላይ ዘግናኝ ጥቃቶችን ፈጽሟል።
በ27 ዓመቷ ወጣት ላይ ቡድኑ የፈጸመው ድርጊት የቡድኑን ማንነት ያሳየም ሆኗል።
ባለቤትሽ የፋኖ አባል ሆኖ ወደ ግንባር ሄዷል በሚል አራት ሆነው ወደ ቤቷ በመሄድ ኢ-ሰብዓዊ ድርጊትን ፈጽመውባታል።
በአራት አመት ልጇ ፊትም በመደብደብ በቡድን እንደደፈሯት ተናግራለች፡፡
ልጇን አንተም ስታድግ ትዋጋናለህ በማለት እንዳዋከቡትና ከአልጋ ላይ እንደወረወሩት የምትናገረው ተጎጂዋ ቤቷ ውስጥ ጥይት በመተኮስ አስፈራርተውናልም ብላለች።
በተፈጸመባት ጥቃትና ድብደባ የ5 ወር ጽንሷ እንደተቋረጠ የምትገልጸው ወጣቷ ለከፍተኛ የጤናና ስነ ልቦና ቀውስ መጋለጧን ተናግራለች።
በደብረ ብርሃን ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በህክምና ላይ የምትገኘው የ27 ዓመቷ ወጣት የሽብር ቡድኑ ታጣቂዎች በልጇ ፊት የፈጸሙባትን ጥቃት ለመርሳት እንደተቸገረችም ገልፃለች።
የዞኑ ሴቶች ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ ሀላፊ ወይዘሮ የለም ሸዋ በቀለ፥ የህወሃት ሽብር ቡድን በሰሜን ሸዋ ዞን ወሯቸው በነበሩ አካባቢዎች በሴቶችና ህጻናት ላይ ታሪክ ይቅር የማይለው ጥቃት አድርሷል ያሉ ሲሆን፥ ድርጊቱም የቡድኑን አረመኔያዊነት ያሳየ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በሽብር ቡድኑ ጥቃት የደረሰባቸውን ሴቶችና ህጻናት ወደ ህክምና ተቋም በማምጣት የጤናና ስነ ልቦናዊ ድጋፍ እንዲያገኙ እየተደረገ መሆኑን የገለጹት ኃላፊዋ ጥቃት ደርሶባቸው ቤታቸው የተቀመጡ ካሉ ችግሩ ሳይባባስ ወደ ህክምና ተቋም እንዲመጡ ጥሪ አቅርበዋል።
በግርማ ነሲቡ
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

