አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በዋና ዋና ሀገራዊ እና የሀገረ መንግሥት ግንባታን በሚያጠናክሩ ጉዳዮች ላይ ምክክሮች እንደሚያስልጉ መንግሥት በጽኑ እንደሚያምን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ፡፡
የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ከበደ ዴሲሳ ዛሬ በሰጡት መግለጫ፥ ምክክሩ በአንድ ጊዜ ተጀምሮ የሚጠናቀቅ ባለመሆኑ፥ ምክክሩን ለማስጀመር ተቋማዊና ህጋዊ ማዕቀፎችን የማዘጋጀት ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
መቼ፣ ከእነማን ጋር ድርድር ይደረጋል የሚለውን ሥራ የሚያከናውንና የሚያስተባብር እንዲሁም አካታች አገራዊ ምክክር እንዲደረግ እና ይህንኑ የሚያስተባብር ተቋም እንዲገነባና እንዲደራጅ ህጋዊ ማዕቀፉ መዘጋጀቱንም አንስተዋል፡፡
በተለይም ነጻና ገለልተኛ የሆነ ተቋም ማደራጀት ያስፈልጋል ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው፥ ይህንን ለማሳካት ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን እንዲቋቋም ረቂቅ አዋጅ ቀርቦ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ጸድቆ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲፀድቅ በሂደት ላይ ይገኛል ብለዋል፡፡
አገራዊ ምክክሩን አንዳንድ ወገኖች ከወቅታዊ ሁኔታ ጋር በማያያዝ ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ አገራዊ አገረ መንግሥት ግንባታውን ለማጠናከር የታሰበውን ወደ ጎን በመተው ከአሸባሪው ቡድን ጋር ድርድር የታሰበ አድርጎ የሚያቀርቡ መኖራቸውን ተናግረዋል፡፡
ይህም ፍጹም የተሳሳተ መረጃ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
አገራዊ የምክክር መድረኩ የቆየ እንጂ፤ አሁን ከጦርነቱ ጋር ተያይዞ የመጣ ሃሳብ አለመሆኑን በመግለጫቸው አንስተዋል፡፡
በዮሐንስ ደርበው
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

