አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በካማሺ ዞን በካማሺ ከተማ ሄና ቀበሌ ሁሩንጉ ጎጥ በጸረ-ሠላም ኃይሎች ታፍነው የነበሩ 62 ሰዎች የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ባካሄዱት አሰሳና ኦፕሬሽን ከጠላት እጅ ወጥተው ወደ ማህበረሰቡ መቀላቀላቸውን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
የአሰሳና የኦፕሬሸን ስራውን የመሩት የክልሉ ፓሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ምስጋና እንጂፋታ እንደገለጹት÷ ለሃገርና ለወገን ደንታ የሌላቸው የአሻባሪው ህወሃት ተላላኪዎች ማህበረሰቡን በማታለል፣ በማስገደድና በማፈን ላልተገባ ዓላማ እያሰለፏቸው ነው፡፡
የታፈኑ የማህበረሰብ ክፍሎችን የጸጥታ ኃይሉ ከፀረ-ሰላም ሀይሎች እጅ ለማስለቀቅ ለተደረገው ትግል አመስግነው፥ ንጹሃንን ከጠላት የመነጠል ስራ ተጠናክሮ እንዲቀጥልም ጠይቀዋል።
በተደረገው አሰሳና ኦፕሬሽን 62 ሰዎችን ከጠላት እጅ በማስለቀቅ ወደ ማዕከል እንዲገቡ መደረጉን ጠቅሰው፥ ቀሪ በየአካባቢው በግዳጅ የታፈኑ ሰዎች በሠላማዊ መንገድ ወደ መንግሥት እንዲመጡ መንግስትም አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደረግላቸው መገለፁን ከክልሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳይ ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

