Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በምስራቅ ወለጋ ዞን 20 የሸኔ አባላት እና የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በምስራቅ ወለጋ ዞን ጉቶ ጊዳ ወረዳ 20 የሸኔ ሽብር ቡድን አባላት እና የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ አስታወቀ፡፡
የጉቶ ጊዳ ወረዳ ፖሊስ ጽህፈት ቤት ሃላፊ ዋና ሳጂን ከተማ ኦልጂራ እንደገለጹት፥ በቁጥጥር ስር ከዋሉት 20 የአሸባሪው ሸኔ አባላት መካከል 7ቱ መንግስት ያቀረበውን ጥሪ በመቀበል በሰላም እጃቸውን የሰጡ ናቸው፡፡
ከሽብር ቡድኑ አባላት በተጨማሪም 16 ክላሽንኮቭ ጠብመንጃ፣ 11 ኋላ ቀር የጦር መሳሪያ እና ጥይቶች መያዛቸውን ነው የገለጹት፡፡
ከዚህ ባለፈም ለሽብር ተግባር ሊውሉ የነበሩ የተለያዩ አልባሳት እና ብሮች መያዛቸውን ከኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

 

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version