Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን እና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ለሰራዊቱ ከ5 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን እና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ለመከላከያ ሰራዊት 5 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አድርገዋል፡፡

የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶክተር መኩሪያ ሃይሌ÷ የጥፋት ቡድኑ ህወሓት በንጹሃን ዜጎች ላይ ታሪክ ይቅር የማይለው ግፍ መፈጸሙን አስተዋል፡፡

ይህን ለመቀልበስም መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ከዳር እስከ ዳር በመነቃነቅ ደጀንም ዘማችም ሆኗል፤ እኛም ከጀግኖቻችን ጎን በመሆን ድጋፋችንን አሳይተናል ብለዋል፡፡

በዚህ መሰረትም ኮሚሽኑ ከኢትዮጵያ ስራ አመራር ኢኒስቲቲዩት ጋር በመተባበር ከ2 ሚሊየን ብር በላይ የጥሬ ገንዘብ እና ግምቱ 400 ሺህ ብር የሚደርስ የደረቅ ሬሽን ድጋፍ ማድረጉን ጠቁመዋል፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ስራ አስፈፃሚው አቶ ሽፈራው ተሊላ፥ ተቋሙ ተቋራጮችን እና አምራቾችን በማስተባበር 3 ሚሊየን ብር ድጋፍ ማድረጉን ተናግረዋል፡፡

ከድጋፉ ባሻገርም ሰራተኞች ቀን እና ሌሊት እየሰሩ መከላከያ ነፃ ያወጣቸውን አካባቢዎች እግር በእግር እየተከታተሉ በጦርነቱ ምክንያት ጨለማ ውስጥ የገቡ ወገኖችን በማይታመን ፍጥነት ብርሃን እዲያገኙ እያደረጉ ማለታቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የመከላከያ ፋይናንስ ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ወይዘሮ ማርታ ሉዊጂ በበኩላቸው÷ተቋማቱ የተለመደውን የደጀንነት ተግባር በመፈጸማቸው ምስጋና አቅርበዋል፡፡

Exit mobile version