Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የህወሓት አሸባሪ ቡድን ከ60 በላይ የጅምላና የተናጥል መቃብሮች በትምህርት ቤት ግቢ ውስጥ ቀብሮ ሸሽቷል – ትምህርት ሚኒስቴር

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የህወሓት አሸባሪ ቡድን ከ60 በላይ የጅምላና የተናጥል መቃብሮች በትምህርት ቤት ግቢ ውስጥ ቀብሮ መሸሸቱን የትምህርት ሚኒስቴር ገለጸ፡፡

የህወሓት ወራሪ ቡድን በደቡብ ወሎ ገርባ አልነጃሽ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከ60 በላይ የጅምላና የተናጥል መቃብሮች በትምህርት ቤት ግቢ ውስጥ ቀብሮ ሸሽቷል፡፡

የአማራ ክልልና የአፋር ክልልን የወረራው አሸባሪውና ወራሪው የትህነግ ቡድን በደቡብ ወሎ የገርባ አልነጃሽ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤትን የጦር ካምፕና የቁስለኞች የህክምና ማዕከል አድርጎት ቆይቷል፡፡

ቡድኑ በህብረተሰቡ ተሳትፎ የተገነባውን ትምህርት ቤት የጦር ካምፕ ከማድረጉም ባሻገር በውስጡ የነበሩትን ኮምፒውተሮች ዘርፏል፤ መጽሃፍትን በሙሉ አቃጥሏል ፤ የቤተ ሙከራ ክፍሎችንም አውደሟቸው መሄዱም ተገልጿል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም አሸባሪው ቡድን የትምህርት ቤቱን ግቢ ከእውቀት ገበያነት ወደ መካነ መቃብርነት መቀየሩ የተገለጸ ሲሆን፥ ትምህርት ቤቱ ውስጥ የሞቱ ወታደሮቹን አስከሬን እንደቀበረበት ተነግሯል፡፡

ከ60 በላይ የጅምላና የተናጥል መቃብሮች በትምህርት ቤቱ ግቢ ውስጥ ቀብሮ መሸሹ የተገለጸ ሲሆን፥ በዚህም ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት መጥተው ለመማር የስነ ልቦና ጫና ደርሶባቸዋል ፡፡

መንግስት በትምህርት ቤታቸው ያሉ መቃብሮችን አንስቶ ወደ ቀብር ቦታ ተውስደው እንዲቀበሩ ትብብር እንዲያደርግላቸው ነዋሪዎች መጠየቃቸውን ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version