አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከገረገራ እስከ ጋሸና ያለውን የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ጥገና በቀጣዮቹ አራት ቀናት ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሰሜን ምዕራብ ሪጅን የማስተላለፊያ መስመሮችና ማከፋፈያ ጣቢያዎች ኦፕሬሽን ቢሮ አስታወቀ፡፡
የቢሮው ዳይሬክተር ውበት አቤ እንደገለፁት፥ ከዚህ ቀደም ጉዳት ደርሶባቸው ከነበሩ የማስተላለፊያ መስመሮች በተጨማሪ አምስት ቦታዎች ላይ ጉዳት ያጋጠመ ሲሆን፥ ሦስቱ ከባድ የመበጣጠስ ጉዳት የደረሰባቸው ናቸው፡፡
የደረሱትን ጉዳቶች የመጠገን ሥራ በርብርብ እየተከናወነ መሆኑን የጠቀሱት ዳይሬክተሩ በቀጣዮቹ አራት ቀናት ውስጥ ሥራው ሊጠናቀቅ እንደሚችል ከኤሌክትሪክ ኃይል ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

