አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) “ስጦታችን ለፈረሰው ትምህርት ቤታችን” በሚል መሪ ቃል በጦርነቱ ምክንያት ለወደሙ ትምህርት ቤቶች የመጽሐፍ ማሰባሰብ መርሐ ግብር ዛሬ ተጀመረ፡፡
የአዲስ አበባ ወጣቶች ማኅበር፣ ጓደኝነት ለመልካምነት የበጎነት ስብስብ እና ጃዕፋር መጽሐፍት በጋራ በመተባበር መርሐ ግብሩን አዘጋጅተውታል፡፡
መጽሐፍቱ የሚሰበሰቡበት ቦታዎች ይፋ መደረጉንም ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ያገኘነው መረጃ ያመለክታለክል፡፡
የመጽሐፍት መሰብሰብ ሂደቱ ከዛሬው ቀን ጀምሮ እስከ ጥር 30 ድረስ የሚካሄድ እንደሆነም ተገልጿል።
አሰልጣኝ አስራት ኃይሌ እና ደራሲ ዘነበ ወላ የዚህ በጎ ተግባር አንባሳደር ሆነው ተመርጠዋል።
የትምህርት ጉዳይ የሁሉም ጉዳይ ነው ያሉት አስተባባሪዋቹ በአማራ እና በአፋር ክልል በጦርነት ምክንያት ከትምህርት ገበታቸው የተፈናቀሉ ተማሪዋች ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱ የሚደረገውን ጥረት የትምህርት ግብአትን በመሰብሰብ እንዲያግዙ ጠይቀዋል።
የበጎ ተግባሩን ለማገዝ የሚፈልጉ ዜጎችም በአዲስ አበባ በሚገኙ የመንግሥት እና የግል ትምህርት ቤቶች በተመረጡ የመጽሐፍት መደብሮች እና የገና በዓል ባዛር በሚዘጋጅባቸው ስፍራዎች በመሄድ መጽሐፍትን ማስረከብ ይችላሉ ተብሏል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

