Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በ”1 ሚሊየን ወደ ሀገር ቤት” ዘመቻ ዳያስፖራዎች ንቁ ተሳትፎ የሚያደርጉባቸው የተለያዩ መርሃ ግብሮች ተዘጋጅተዋል

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በ”1 ሚሊየን ወደ ሀገር ቤት” ዘመቻ ኢትዮጵያዊያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያዊያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች ሲመጡ ንቁ ተሳትፎ የሚያደርጉባቸው የተለያዩ መርሃግብሮች መዘጋጀታቸው ተገለፀ፡፡

ከታላቁ ወደ ሀገር ቤት ጉዞ ጥሪ ጋር በተያያዘ ሚሲዮኖች እያከናወኑ ባሉት ተግባራት ላይ የበይነ መረብ ውይይት ተካሂዷል፡፡

በውይይቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ፥ ጥሪው የታለመለትን ዲፕሎማሲያዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዓላማዎችን ማሳካት ይችል ዘንድ ሚሲዮኖች ከብሔራዊ ኮሚቴው በወረደላቸው ዕቅድ መሰረት እስካሁን ካደረጉት እንቅስቃሴ በተጨማሪ ፈጠራና ቴክኖሎጂ መር የሆነ የቅስቀሳና ዓላማውን የማስተዋወቅ ሥራ ማካሔድ እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

ኢትዮጵያውያን ፣ትውልደ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች ወደ ኢትዮጵያ ሲገቡ ንቁ ተሳትፎ የሚያደርጉባቸው የተለያዩ መርሃ ግብሮች በብሔራዊ ኮሚቴው መዘጋጀቱንም ጠቅሰዋል፡፡

ከፀጥታ አኳያም እንግዶቹ ምንም አይነት ስጋት እንዳያድርባቸው የሚያደርግ ሥራ በፀጥታ ሀይላት በኩል የተቀናጀ ዝግጅት መደረጉን አንስተዋል።

ከተናጥላዊ ድጋፍ በተጨማሪም የወደሙ የትምህርትና የጤና ተቋማትን ለመገንባትና ለመጠገን ዕቅድ ያላቸውን ዳያስፖራዎች ማበረታታት፣ አዳዲስ ሀሳብ እንዲያመጡ ደግሞ ቅስቀሳ ማድረግ ከሚሲዮኖች የሚጠበቅ መሆኑንም አብራርተዋል።

የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር መሐመድ እንድሪስ፥ ከዳያስፖራው የሚነሱ ጥያቄዎችን ለመመለስ እየተሰራ መሆኑን አንስተው በእስካሁኑ ሂደትም ከቪዛ፣ ጉምሩክና የአየር ትራንስፖርት ጋር በተያያዘ ለቀረቡ ጥያቄዎች ምላሽ መሰጠቱን ገልጸዋል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version