አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በደብረ ብርሃን ከተማ ተፈናቃዮች ተጠልለውባቸው በነበሩ ትምህርት ቤቶች ከሰኞ ጀምሮ የመማር ማስተማር ሂደቱ እንደሚቀጥል የከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ፅህፈት ቤት ሀላፊ ብርሀኑ ይመር ገለጹ፡፡
ኃላፊው ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለፁት፥ በከተማው ውስጥ ህወሓት በከፈተው ጦርነት ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ ዜጎች በመጠለያነት ሲያገለግሉ የነበሩ ትምህርት ቤቶች ከሰኞ ጀምሮ በተያዘላቸው መርሃ ግብር ሁሉም የመማር ማስተማር ሂደታቸውን ይቀጥላሉ።
አሁን ላይም ለትምህርት ቤቶቹ ተገቢው የፅዳት ስራ ተሰርቶላቸው እና መሟላት ያለባቸው ቅድመ ሁኔታዎች ስለተሟሉ ተማሪዎች በመማሪያ ክፍላቸው በመገኘት ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ አቶ ብርሃኑ ጥሪ አቅርበዋል።
በደብረ ብርሀን ከተማ ሶስት አንደኛ ደረጃ እና ሶስት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች፥ በአጠቃላይ በስድስት የትምህርት ተቋማት ተፈናቃዮች ተጠልለው ይገኙ እንደነበር ይታወሳል፡፡
በኤልያስ ሹምዬ
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

