Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በአማራ እና በአፋር ክልሎች የሰብዓዊ ዕርዳታ ለማድረስ እየሠራሁ ነው – የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፋርና አማራ ክልሎች በአሸባሪው ህወሓት ሰብዓዊ ቀውስ ለደረሰባቸው ዜጎች እርዳታ እንዲደርስ እየተሰራ መሆኑን የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን አስታወቀ።
የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር ሀይድሩስ ሀሰን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት፥ በአሁኑ ወቅት በሁለቱም ክልሎች አስቸኳይ የሰብዓዊ እርዳታ እና ድጋፍ ለማድረስ የምግብ አቅርቦት ግዢ ከውጪ ሀገር ጭምር እየፈጸምን ነው ብለዋል።
ምክትል ኮሚሽነሩ እንደገለጹት ድጋፉ በተለይ በአሸባሪ ቡድኑ ቁጥጥር ስር በቆዩት የአማራ ክልል አከባቢዎች የቅድመ ምላሽ አስቸኳይ የምግብ ድጋፍ በተለየ ትኩረት እንዲደርሳቸው እየተሰራ ነው።
በተጨማሪም የሰብዓዊ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸውን ዜጎች በተገቢው መልኩ ተደራሽ ለማድረግ የጉዳቱን መጠን የሚያጣራ ግብረ-ኃይል እንደተቋቋመና ተፈናቃይ ዜጎች ወደሚገኙበት ስፍራ እንደተላከ ነው ኮሚሽነር ሀይድሩስ ሀሰን የተናገሩት።
በአሁኑ ወቅት ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ ዜጎች በሀገር ውስጥ እና በውጪ ሀገር የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ድጋፍ እያደረጉ ይገኛልም ብሏል ኮሚሽነሩ፡፡
ድጋፉ በተገቢው ሁኔታ ለተጎዱ ዜጎች እንዲደርስም ከግለሰቦች እና ከድርጅቶች የሚገኘው ድጋፍ ወደ ኮሚሽኑ መምጣት እንዳለበትና በአንድ ማዕከል ሊሰበሰብና ሊዳረስ እንደሚገባም አሳስበዋል።
በአዳነች አበበ
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version