Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የሀሰት መረጃ በኢትዮጵያ ዲፕሎማሲ ላይ ያሳደረው ጫናና መፍትሄው በሚል ርዕሰ ምክክር እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ “የሀሰት መረጃ በኢትዮጵያ ዲፕሎማሲ ላይ ያሳደረው ጫና እና መፍትሔው” በሚል ርዕስ የምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው።

በመርሃ ግብሩ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማህበራዊ ጉዳዮች አማካሪ ሙሐዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ እና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ ዶክተር ኦባንግ ሚቶ እንዲሁም ሌሎች ተሳታፊዎች ተገኝተዋል።

በመድረኩ የመክፍፈቻ ንግግር ያደረጉት የጠቅላይ ሚንስትሩ የማህበራዊ ዘርፍ አማካሪ ሙአዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት አሜሪካን ጨምሮ የአንዳንድ ምዕራባዊያን ሀገራት ሚዲያዎች ለአሸባሪ የህወሃት ቡድኑ የወገነ ዘገባ ማሰራጨታቸው የተለመደ መሆኑን እያየን ነው ብለዋል፡፡

በተለይም በዚህ የህልውና ዘመቻ ወቅት መንግስት የሀገርና የህዝብን አንድነት ለማስጠበቅ የሚሰራውን ወደ ጎን በመተው ለአሸባሪ ቡድኑ የወገነ ዘገባ ማሰራጨታቸው የተለመደ መሆኑን እያየን ነው ብለዋል።

አሸባሪ ቡድኑ ግፍና በደል የተፈፀመበትን የአማራና የአፋር ህዝብ ወደ ጎን በመተው ጩኸታቸው ሁሉ ለወራሪው መሆኑ አሳዛኝ ድርጊት መሆኑን ገልጸዋል።

ይሄን እኩይ ተግባራቸውን የሚፈፅሙትም ሳያውቁ ሳይሆን ሆን ብለው ኢትዮጵያን ለማንበርከክ የያዙትን ግብ ለማሳካት ያለመ መሆኑን ተናግረዋል።

በሀገሪቱ የሚገኙ ምሁራንም ይሄን እኩይ ድርጊታቸውን በአግባቡ በመገንዘብ እንደዚህ ዓይነት ተከታታይ ጉባኤ በማዘጋጀትና መፍትሄ በመዘየድ ሃላፊነታቸውን እንዲወጡ መልዕክት አስተላልፈዋል።

የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ፍሬው ተገኘ በበኩላቸው፤ አሸባሪው ህወሃት በየጊዜው የሚነዛው የሃሰት መረጃ በማህበረሰባችን ላይ ምን ያህል ጉዳት እንዳደረሰ የቅርብ ጊዜ ትውስታችን ነው ብለዋል።

በሚነዛው የሃሰት ፕሮፓጋንዳ ህብረተሰቡ ሃብትና ንብረቱን እየተወ በመፈናቀሉ ለተለያዩ ችግሮች መዳረጉን አውስተው፤ይሄን እኩይ ድርጊት በጋራ መመከት ይገባል ማለታቸዉን ኤዜአ ዘግቧል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version